Tuesday, April 23, 2013
ትንሽ ምክር ቤጤ ለወዳጄ ልጅ ተክሌ
በኢሳት ላይ ያለህን ቅሬታ በአውራባ ታይምስ ድህረ ገጽ ላይ ወጥቶ አነበበኩት። የጹሑፉ ፍሬ ነገር አላስገረመኝም ወይም
በቀረበው ሐሣብ ላይ ቅሬታ የለኝም።ቅሬታ የሚኖርብኝና ይህንን እንድጽፍ ያነሳሳኝ: ግን: ቅሬታውን ለማቅረብ
የመረጥከውመንገድ ነው።
ልጅ: ተክሌ:እኔ እስከማውቅህ ድረስ ለኢሳት ቀረቤታ ያለህና ለኢሳት ሥራ ዘወትር በትጋት: አስተዋጽኦ: በማድረግህ: ስለሆነ:
ለኢሳት ያለህን አስተያየት ወይም ቅሬታ ለስራ:ባልደረቦችህ:ለድርጅቱ ሃላፊዎች ወይም ለቦርዱ ማቅረብ: ነበረብህ ባይ ነኝ።
ይህን በግል ብነግርህ መልካም ነበር። ሆኖም ያአንተ ጹሑፍ በአደባባይ: በመውጣቱ: እኔም ምክሬን በአደባባይ ላደርገው ብዬ
ነው።ሌሎቹም እንዲሰሙኝ።
ይህ የመናገር ነፃነቴ ነው ልትለኝ ትችላለህ:: ልክ ነውም። ግን እኮ የመናገር ነፃነት
የሚመጣው ከሃላፊነት ጋራ ነው። ያውም “self -censorship” ከሚሉት:
ሃላፊነት: ጋር ። ላብራራ: በአንድ ሰው ፊት ላይ ጉድፍ ቢኖር የተለያዩ ሰዎች
በተለያየ መንገድ ይህን በሰውዬው ላይ ያለውን:ጉድፍ: ለሰውዬው ለመንገር
ይጥራሉ።
ሕፃናት የሆኑ እንደሆነ ጉድፉን ያዩት በጣም ግልጽ በሆነ ግን ሰውዬውን
በሚያሳፍር መንገድ :በሰው: መሐል: አንተ ፊትህ: ላይ ቁሻሻ: አለብህ ብለው
ይናገራሉ። ልጅ ያየው እንደሚባለው፤‘ትልቅ ሰው’ የሆነ እንደሆነ ጉድፉን ያየው በቀጥታ ተናግሮ ሰውዬውን ከማሳፈር
የተለየዩ ዘዴዎችን ተጠቅሞ ለሰውዬው የጉድፉን መኖር ሊጠቁመው ይችላል።
አየህ: ልጅ ተክሌ ሁለቱም መንገዶች: ሰውዬው ጉድፉን: እንዲያነሳ ለማድረግ የተደረጉ ናቸው ግን አቀራረባቸው የተለየ
ነው።አንተም ሁለተኛውን:መንገድ: ተጠቅመህ:ቢሆን: ኖሮ ምንኛ: ባደነቅሁ ነበር።በተለይም :በአሁኑ: ሰአት: ጠላቶቻችን:
በእቶን:እሳት: በእሳት: በሚለበለቡበትና:ያን:ለማጥፋት:በሚቅበዘበዙበት:ጊዜ:: ግን: አልሆነም:: ወደፊት: እንደሚታረም:
ግን:ተስፋ:አደርጋለሁ::
ልጅ ተክሌ ጹሑፎች ካናደዱ ወይም ካለስጨበጨቡ አይዋጥልኝም ብለሃል።እኔ በዚህ አልስማማም። ምክንያቱም እንዲህ
ዓይነቱ ጹሑፎች ስሜታዊነትና:ጊዜያዊነት: ያጠቃቸዋልና:: በኔ: እምነት: ጽሁፎች:አይምሮን የሚኮረኮሩ (thought
provoking) እና ገንቢ ቢሆኑ: ምርጫዬ: ነው፤ ሆኖም: ግን: ምርጫህን: አልጋፋም።እንዲያው: በውልና ጥቅምና ጉዳቱን
ባመዛዘነ መንገድ ይሁን ከሚል አንፃር እንጂ::
ልጅ ተክሌ እንደያው ድፍረት ባይሆንብኝ ለወዲሁም ታላቅህ ነኝ ና፤ ምክሬን ሰማኝ ኢሳቶች ጥፋት ካለባቸው( ፍጹም
ናቸውም ብዬ ለመከራከር አልከጅልም) እባክህ በጆሮ አቸው ሹክ በላቸው: ደግሞም: ከእኔ ይበልጥ: ቅርበት አለህና! እንዲህ
በአደባባይ መናገሩ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። እኔም አንተም ለጠላቶቻችን ቅጣት ያህልም ቀዳዳ መስጠት የለብንም ብዬ
በማሰብ በቅን ልቦና የሰጠሁት አስተያየት ስለሆነ ምክሬ ትቀበለዋለህ ብዬ አስባለሁ።
የኢሳትም አስተዳደርም ግልጽ የሆነ የቅሬታ መስሚያና ማስወገጃ መንገድ (complaint resolution process)
አለው ብዬ ስለማስብ በዚያ መጠቀሙ ለሁላችንም ይበጃል: እላለሁ።
ታዛቢ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment